አዲስ ዘመን ሀሙስ ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ቁጥር 33/2017 እና ሃራጅ ቁጥር 18/2017
በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ተወርሰው የሚገኙ ብዛት ያላቸው ክር (Thrade) ኤሌክትሮኒክስ ፣
የተሽከርካሪ መለዋወጫ ፣ ኮስሞቲክስ ፣ ሸቀጣሸቀጥ እና 3 ተሸከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ኤሌክትሮኒክስ
፣ ሸቀጣሸቀጥ ፣ ፣5 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች እና 1 ተሸከርካሪ በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶችን የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጫረታው
መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን:
1.በአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው
ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራን
እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው ፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን
ለግልፅ ጨረታው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት እና ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው
በሚካሄድበት ቀን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
2.በተ.ቁ 1 ላይ የተጠቀሰው መስፈርቶች ቢኖርም ሞተር ሳይክሎች እና ተሽከርካሪዎቹ ላይ ማንኛውም እድሜው
ከ8 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ እና 100 ብር የገዛበትን ደረሰኝ በመያዝ ያለ ቅድመ ሁኔታ ጨረታው ላይ
መሳተፍ ይችላል፡፡
3.በተ.ቁ 1 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ
ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገብ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
4.የግልፅ እና ሃራጅ ጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ
ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት
ከ2፡00 6፡00 ሰዓት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሃሳብና ዋስትናዎች
አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመግዛት በጨረታ የወጡትን ዕቃዎችን ማየት የምትችሉ መሆኑን
እንገልፃለን፡፡
5.በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ
(5%) እና ሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩበት ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፡- ለምድብ 01 ተሸከርካሪ መለዋወጫ ብር
14,500.00 (አስራ አራት ሺህ አምስት መቶ) ለምድብ 02, የተሽከርካሪ መለዋወጫ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ለምድብ
03, ኤሌክትሮኒክስ ብር 73,000.00 (ሰባ ሶስት ሺህ) ለምድብ 04, ኤሌክትሮኒክስ ብር 384,000.00 (ሶስት መቶ ሰማኒያ
አራት ሺህ) ለምድብ 05, ተሸከርካሪ መለዋወጫ ብር 88,000.00 (ሰማንያ ስምንት ሺህ) ለምድብ 06, ተሽከርካሪ መለዋወጫ
ብር 138.000.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ) ለምድብ 07, ኤሌክትሮኒክስ ብር
145.500.00 (አንድ መቶ አርባ አምስት ሺህ አምስት መቶ) ለምድብ 08, ኤሌክትሮኒክ ብር
88,200.00 (ሰማንያ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ) ለምድብ 09,ሸቀጣሸቀጥ ብር 4,200.00/አራት ሺህ ሁለት መቶ | ለምድብ
10, ኤሌክትሮኒክስ ብር 281,200.00(ሁለት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ) ለምድብ 1,ኮስሞቲክስ ብር
13,100.00 (አስራ ሶስት ሺህ አንድ መቶ) ለምድብ 12, ተሸከርካሪ መለዋወጫ ብር 331,200.00 (ሶስት መቶ ሰላሳ አንድ
ሺህ ሁለት መቶ) ከምድብ 13 - 5 ለእያንዳንዱ ምድብ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ብር 25,000.00 (ሀያ አምስት ሺህ) እና
ለምድብ 16 ተሸከርካሪ ብር 76,500.00 (ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO)
Customs Commission Adama Branch Office ስም በማሰራት ለግልፅ ጨረታ በተራ ቁጥር 1 ላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች
ጋር በማያያዝ እንድታስገቡ እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት እለት ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
6.በጨረታ ሽያጭ የእቃው አስመጪ ወይም ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡
7. በግልፅ ጨረታ ለሽያጭ ለቀረቡ ዕቃዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚገኝበት የቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን አስተዳደር
የስራ ሂደት ቢሮ በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው ቢሮ ግቢ በመገኘት በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን የጨረታ
ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO፣የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር 1 ላይ ከተጠቀሱት ሌሎች ሰነዶች ጋር በፖስታ በማሸግ
ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለጨረታ ኮስሞቲክስ በተዘጋቸው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡እንዲሁም ሃራጅ ጨረታ ለመጫረት ሲፒኦ
ያሰራችሁ ተጫራቾች ከሌሎች ሰነዶች ጋር ጨረታው በሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት ይዛችሁ መገኘት አለባችሁ፡፡
8.በግልፅ ጨረታ እና በሀራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ ዳት አከባቢ በፍልቅልቅ
ግሮሰሪ ወደ ውስጥ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ እንዲሁም
ተሽከርካሪዎቹ በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አ/ማ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው መጋዘን ቁጥር 10 ስለሚገኙ ለግልፅ ጨረታው
ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ
4፡15 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ነገር ግን ስምንተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት
በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ ለሃራጅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ
በኋላ በስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታ የሚጀመር ሲሆን፤ ስድስተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ
ቀን የሚካሄድ ይሆናል፡፡
9.የግልፅ ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቦታ እና የሀራጅ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ የቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን
አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው ቢሮ ግቢ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም
ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይካሄዳል፡፡
10. ሐራጅ ጨረታ እቃዎቹ፣ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎቹ እና ተሸከርካሪዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነለት ስለሆነ
የመነሻ ዋጋው በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል፡፡
11.በኦርጅናል ሰነድ ያልተሞላ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
12. ማንኛውም በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይም የሌላ ተጫራችን
ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፡፡
13.ለግልፅ ጨረታ ከመነሻ ዋጋ በታች ወይም እኩል የመነሻ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበ ተጫራቾ ከጨረታ ይሰረዛል፡፡
14.አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ
ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
15.አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን
ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
16.ከላይ በተ/ቁ 5 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች
ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
17.ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች እና ተሸከርካሪዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት
ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
18.ማንኛውም ተጫራች 100 (አንድ መቶ) ብር ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ ለግልፅ ጨረታ ከሌሎች ሰነዶች
ጋር አያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን፤ ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ከሌሎች ሰነዶች ጋር ይዞ መገኘት
አለበት፡፡
19.ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
20.ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ
የማንቀበል መሆኑን አናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡- 022-11-84-29 እና 022-21-89-25 ደውሎ መጠየቅ
ይቻላል፡፡
አዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት