አዲስ ዘመን ሀሙስ ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
በቆሎ ስመሸጥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ መጠኑ 200,000 ኩ/ል 1ኛ ደረጃ በቆሎ
በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ መቀሌ ፣ነቀምት እና ሻሸመኔ መጋዘን የሚገኝ ሲሆን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች ብቻ በግልፅ ጨረታ
አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ
|
እህሉ የሚገኝበት ቦታ
|
የእህል ዓይነት
|
መጠን በኩ/ል
|
የጥራት ደረጃ
|
እህሉ የሚገኝበት መጋዘን
|
እህሉ የሚውለው አገልግሎት
|
1
|
መቀሌ
|
በቆሎ
|
25,172.20
|
1ኛ ደረጃ
|
ቁ1
|
ለሰው ምግብነት
|
2
|
ባኮ
|
በቆሎ
|
23,907.05
|
1ኛ ደረጃ
|
ቁ4
|
ለሰው ምግብነት
|
3
|
ሻሸመኔ
|
በቆሎ
|
3,698.02
|
1ኛ ደረጃ
|
208/00/08
|
ለሰው ምግብነት
|
4
|
ሻሸመኔ
|
በቆሎ
|
7,975.25
|
1ኛ ደረጃ
|
208/00/08
|
ለሰው ምግብነት
|
5
|
ሻሸመኔ
|
በቆሎ
|
35,175.69
|
1ኛ ደረጃ
|
208/00/07
|
ለሰው ምግብነት
|
6
|
ቢሾፍቱ
|
በቆሎ
|
5,510.00
|
1ኛ ደረጃ
|
ቁ3
|
ለሰው ምግብነት
|
7
|
ቢሾፍቱ
|
በቆሎ
|
3,992.00
|
1ኛ ደረጃ
|
ቁ5
|
ለሰው ምግብነት
|
8
|
ሚቸልኮት
|
በቆሎ
|
49,235.79
|
1ኛ ደረጃ
|
ቁ 203
|
ለሰው ምግብነት
|
9
|
ሚቸልኮት
|
በቆሎ
|
45,334 00
|
1ኛ ደረጃ
|
ቁ 128
|
ለሰው ምግብነት
|
ድምር
|
200,000
|
|
|
|
በዚህ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው በእህል ጅምላ ወይም ችርቻሮ ንግድ፣ በምግብ ማቀነባበር የታደሰ ንግድፈቃድ፣
የንግድ ምዝገባ ያላቸው እና በመኖ ማቀነባበር በመኖ ጅምላና ችርቻሮ ንግድ፣ በእንሰሳት ማድለብ፣ በዶሮ እርባታ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት
ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
2. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ከዋናው መ/ቤት (አዲስ አበባ) ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ
11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡30 እስከ 6፡30 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል
መግዛት ይችላሉ፤ (አድራሻው ከስር ተገልጿል)
3. በቆሎውን ተጫርተው መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ
ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት /ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት- 2፡30 – 6፡30 እና ከሰዓት 7፡30 – 11፡00 እና ቅዳሜ ከ
2፡30 - 7፡00 / በመገኘት እህሉ በሚገኝበት መጋዘን በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ፣
4. ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ብር
100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በዘርፉ ስም (የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ ወይም
Grain and Coffee Trading Business Unit) በሚል ብቻ የተሠራ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ
አለባቸው፤
5. የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ያለስርዝ ድልዝ በመሙላት በፖስታ በማሸግ
ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. በግልፅ የማይነበብ ትክክለኛውን የዋጋ አቀራረብ ሥነ ስርዓት ያልተከተለ የመጫረቻ ሠነድ ውድቅ የሚደረግ
ሲሆን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ላይ ስርዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
7. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ሰነዳቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ
የጨረታ ቁጥር 05/2017 በማለት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት የሥራ ቀናት ክፍት
ሆኖ አስራ ስድተኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 004 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. አሸናፊ ተጫራች ውል ሲፈርም የውል ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 10% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ
የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ መቻል አለበት፣
9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ
አስራ ስድስተኛ የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር
004 ይከፈታል፡፡
10.ተጫራቾች ምርቱን በአካል ቀርበው በማየት ምርቱ ባለበት ደረጃ ለመረከብ ተስማምተው ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል፤
11.ተጫራቾች ከላይ ከተ/ቁ 1 እስከ 9 ከተጠቀሱት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መርጠው መጫረት ይችላሉ፣
12. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤
13.የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት እህሉን ተረክቦ ወደሚፈልግበት ቦታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በራሱ የሚያጓጉዝ
ይሆናል፡፡
14.ዘርፉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን እህልና ቡና ንግድ ዘርፍ
ደብረዘይት መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫ ፊት ስፊት
ስልክ ቁጥር 011 4 16 7884/0114167880
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን