አዲስ ዘመን ዓርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወዞፋ/7/03/17
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የጤና ተቋማት ግንባታ
ቀሪ ሥራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የሚችሉ የሥራ ተቋራጮች፡፡
1. በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተመዝግበው ግብር በመክፈል የ2017 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የታደሰ ብቃት
ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ተ.እ.ታ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ቲን /TIN/ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ
ያላቸው፣ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባ ምሥክር ወረቀት ያላቸው በፌደራል ግዥ እና የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ኤጀንስ በአቅራቢነት ምዝገባ/በበይነ
መረብ የተመዘገበ እና ማቅረብ የሚችሉ ደረጃ GC-7/BC-7 እና ከዛ በላይ የሆኑ፡፡
2. ተጫራቾች ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ወቅተዊ ታክስ ክሊራንስ/ NVALID TAX CLEARANCE/ ሰርቴፊከት
ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ
ሕጋዊ ሠነድ በማቅረብ ለሠነዱ የማይመለስ 1000.00 / አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብረት
አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከ2ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታ ሠነድ ውስጥ በተጠቀሰው መሠረት፡-
-ሎት 1 ጋልቻ ጤና ጣቢያ የባለሙያዎች ማደሪያ 275,000.00 /ሁለት መቶ ሰባ አምስት ሺህ/ ብር
-ሎት 2 ጢዳ ጋርቤ ጤና ጣቢያ የባለሙያዎች ማደሪያ ብር 600,000.00 /ስድስት መቶ ሺህ ብር/፣
-ሎት 3. ቦዲቲ የመጀመሪያ
ደረጃ ሆስፒታል OPD ስሎክ ብር 525,000.00 /አምስት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ብር/
-ሎት 4. ሶዶ ጤና ጣቢያ ፋርማሲ ብሎክ 350,000.00 /ሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/
-ሎት 5. ጋቼኖ ጤና ጣቢያ ፋርማሲ ብሎክ 175,000.00 /አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ ብር
-ሎት 6. ዛባ ጤና ጣቢያ የባለሙያዎች ማደሪያ 325,000.00/ ሦስት መቶ ሃያ አምስት ሺህ/ ብር ከጨረታ
ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሠነድ ኦሪጅናሉን እና ቴክኒካል ሠነድ ኦሪጅናሉን አንድ ላይ በማሸግ እና
2 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ እና ሁሉንም ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ የፕሮጀክቱን
አድራሻና ስም በመጻፍ በዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታው ሣጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ30 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን በ8፡00
ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት በወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር የጨረታ ክፍል ቢሮ ቁጥር 9 ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡
8. ተጫራቾች በጨረታ ማክፈቻ ዋጋና በሂሣብ ማስተካከያ ዋጋ ልዩነት ከ3% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ
ወይም የሚያንስ መሆን የለበትም፡፡
9. ተጫራቾች በዞን እና በሌሎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ሲሠሩ ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው
መሆን አለባቸው፡፡
10. በተጨማሪ እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር
70/2017 እና በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የወጣው የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ መመሪያ ቁጥር
648/2013 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማሻሻያ የያዘ ሴርኩላር ተግባራዊ ይሆናል፡፡
11. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046551 2116 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ